የተመሰረተበት ዓ.ም.
የአባላት ብዛት
የማህበሩ ጠቅላላ ሀብት በሚሊየን ብር
የብድር ጣርያ
ጥቂት ስለ ማህበሩ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰራተኞች የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በኢትዮጵያ ካሉ ግዙፍ ኅብረት ስራ ማህበራት መካከል ዋነኛው ነው፡፡
ማህበሩ በ1974 ዓ.ም በ470 መስራች አባላትና በ10,700.00 መነሻ ካፒታል ተመሰረተ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የአባላት ቁጥር 6000 ሲሆን ጠቅላላ የማህበሩ ሀብት 426,893,821 ነው፡፡
ማህበሩ የብድር አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የብድር ጣርያው 300.00 ነበር አሁን ግን የብድር ጣርያውን 1,000,000 ማድረስ ተችሏል፡፡
የማህበሩ ተልዕኮ
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር ባሉ በሁሉም ካምፓሶች ለሚገኙ የዩንቨርስቲዉ የአስተዳደርና መምህራን ሠራተኞች በማህበሩ አባል ለሆኑ አባላት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግራቸዉን ለመፍታት ዘለቀታዊ የሆነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር አገልግሎት መስጠት
የማህበሩ ራእይ
በ2020 ማኅበሩ የአባላትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር በመቅረፍ በአገሪቱ ካሉ መሰል ኅብረት ሥራ ማኅበራት የተሸለ እና ተምሳሌታዊ የሆነ የፋይናንስ ተቋም መሆን
አገልግሎቶቻችን
ቁጠባ
ብድር
አባላትን ማማከር
ማህበረሰብ አገልግሎት
አባል መሆን ይፈልጋሉ? ልንቀበልዎ ደስተኞች ነን።
ስለ አገልግሎቶቻችን ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ?
ተደጋግመው የተጠየቁ ጥያቄዎች
-
አባል ለመሆን ምንድን ነው የሚጠበቅብኝ?
አባል ለመሆን የሚጠበቅብዎ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋሚ የአካዳሚ ወይም የአስተዳደር ሰራተኛ መሆን ነው።
-
አባል ለመሆን የሚከፈል ክፍያ አለ?
አባል ሆነው ለመመዝገብ የአባልነት 5 እጣ ወይም ሼር በብር 500 መግዛት ያለብዎ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በየወሩ ቢያንስ የወር ደመወዝዎን 1% መቆጠብ አለብዎ።
-
ቁጠባዬን አንዴት ነው የምቆጥበው?
አባል ሆነው ሲመዘገቡ የሚቆጥቡትን መጠን እንዲገልጹ ይጠየቃሉ። በዚሁ መሰረት ደመወዝዎን ለሚያዘጋጀው የሂሳብ ክፍልዎ ተቋሙ በማሳወቅ በዚሁ አግባብ ከደመወዝዎ እየተቀነሰ ወደተቋሙ የባንክ ሂሳብ እንዲተላለፍ ይደረጋል።
-
ተቋሙ የሚከፍለው የቁጠባ ወለድ ስንት ነው?
ተቋሙ የሚከፍለው የቁጠባ ወለድ 7% በአመት ሲሆን የሚሰላው በየወሩ ባለው ጠቅላላ የቁጠባ መጠንዎ ነው።
-
ምንያህል መበደር እችላለሁ?
መበደር የሚችሉት የቆጠቡትን መጠን አራት እጥፍ ሲሆን የብድሩ ጣራው እንደደመወዝዎ መጠን ይወሰናል። የበለጠ ለማወቅ በ 0118125096 ይደውሉ።
-
ለመበደር ምን ማሟላት አለብኝ?
የተቋማችን የብድር አፈቃቀድ ስርአት ቀላልና ቀልጣፋ ነው። ለመበደር የብድር ማመልከቻዎን በአካል በመገኘት ወይም በኦንላይን መሙላት ይጠበቅብዎታል።
ተጨማሪ የተቋማችን የብድር አፈቃቀድ ስርአት ለአባላት ብቻ በተፈቀደው ድረ ገጻችን ላይ በግልጽ ተዘርዝሯል።
ያግኙን
አድራሻ:
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ
ከዋናው የሂሳብ ክፍል አጠገብ
ኢሜይል:
admin@aausavingandcredit.et
ስልክ:
+251 118-12-50-96
